Call us:
+251900668262
|
Mail us for help:
nifasilkpolytech@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Nefas Silk Polytechnic College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Strategic Direction
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Departments
Back
Departments
ICT Departments
Automotive Technology
Business And Finance
Construction Technology
Electrical And Electronics Technology
Hotel And Hospitality
Manufacturing Technology
Textile Garment And Leather
Woodwork Technology
More
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Strategic Direction
Nsptc Colidor Development
Nsptc Colidor Development
18th July, 2026
የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኒክና ሙያ ልህቀትን ከሀገራዊ የልማት ግቦች ጋር በማጣመር ግቢውን ለስልጠና፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራና ለቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ምቹ፣ ጽዱ እና ውብ የማድረግ ታላቅ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል
ኮሌጁ ለሰልጣኞች ፣ ለሰራተኞች ና ለማህበረሰቡ ምቹ ና ሳቢ የስራና የስልጠና የአካባቢን በመፍጠር ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነትን እና የበቃ የሰው ሃይል ምርታማነትን ለማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ እያሰራ ነው።
ኮሌጁ የቴክኒክና ሙያ ልህቀትን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፣ የስራ እና የስልጠና አከባቢን ምቹ ና አግልግሎትን ለማሻሻል የተጠቃሚዎችን ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት እና ምርታማነት ለማሳደግ ያለውን ሚና በመገንዘብ ለዚህ ተግባር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
ዋና ዋና ትኩረቶች
• የአረንጓዴ ስነ-ምህዳር ግንባታ፦ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን በተመረጡ እፅዋት፣ ለምለም ሳሮች እና ውብ አበባዎች የመሸፈን ስራ።
• የማረፊያ እና የፅሞና ስፍራዎች ማዘጋጀት፦ ለሰልጣኞች ከስልጠና ሰዓት ውጭ በነፃነት የሚያጠኑባቸው እና የሚያርፉባቸው ምቹ የንባብ ማዕዘናት መፍጠር።
• የፅዳት እና የስነ-ስርዓት ባህል፦ አጠቃላይ የኮሌጁን ግቢ ውበት ዘላቂ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ እና የፅዳት አጠባበቅን ከኮሌጁ እሴቶች ጋር የማዋሃድ ስራ።
የተቋም ውበት የማንነታችን መገለጫ ብቻ ሳይሆን፣ የቴክኖሎጂ፣ የሃሳብ ፈጠራ እና ጥራት ያለው ስልጠና መሰረት ነው"
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ እንደገለጹት፤ ኮሌጁን በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ስታንዳርዱን የማስጠበቅ፣ የመዘመንና በሁሉም ረገድ የላቀ ውጤት የማስመዝገብ ስራው በቁርጠኝነት ይሰራል ብሏል።
በተጨማሪም ኮሌጃችን ራሱን በማደስና የላቀ የስልጠና አከባቢን በመፍጠር የለውጥ ግንባር ቀደም ምሰሶ መሆኑን ይቀጥላል ብሏል።
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
.