Strategic Direction Industury Extension Support And Acknowledgement

Industury Extension Support And Acknowledgement

18th July, 2026

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርጥ ተሞክሮን የማስፋትና የዕውቅና መርሀ-ግብር ተካሄደ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ ና ክህሎት ቢሮ የንፋስ ስልክ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፍ ከሚደረግላቸው አንቀሳቃሾች መካከል የተመረጡ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ተሞክሯቸውን አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የንፋስ ስልክ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን በለሙያ አቶ ጌታቸው ተፈራ የሞዴል መመልመያ ሰነድ የቀረቡት እንደ ኮሌጅ በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች ማለትም በሒሳብ አያያዝ፣ በካይዘን፣ በክህሎት ክፍተት እና በስራ ፈጠራ ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የገልፁ ሲሆን አቶ ተደለ ሀይሉ የመርሀ-ግብሩ ዋና አላማ የሚደረገውን ድጋፍ ተጠቅመው ውጤት ላመጡ ኢንተርፕራይዞች እውቅና መስጠትና ተሞክሯቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉ ማድረግ ነው ብለዋል።
በንፋስ ስልክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ና ኢ/ኤ አቶ ባህሩ ሻፊ አንቀሳቃሽ ኢንተርፕራይዞች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ በኮሌጅ ደረጃ ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር የባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እና መተባበር ወሳኝ ነው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚያገኙ አንቀሳቃሾች መካከል የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ኢ/ዞች ከቢሮው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ና ኢንኩቤሽን ቡድን መሪ ከሆኑት ከአቶ ተደለ ሀይሉ ና የቴክኖሎጂ ልማት ና ኢ/ኤክስቴንሽን ም/ዲን ከአቶ ባህሩ ሻፊ እጅ የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


.

Copyright © All rights reserved.

Created with