Strategic Direction Business Comptition Closing And Acknowledgement Program

Business Comptition Closing And Acknowledgement Program

22nd July, 2026

ፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የንግድ ስራ ፈጠራ ውድድር ላይ አሸናፊ ለሆኑ አስር ቡድኖች የስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ተሰጠ፡፡

ሐምሌ 15/2018

በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአቶ አብረሃም ኤቢሳ አስተባባሪነት ለሀገር ውስጥ ዜጎችና ለስደተኞች የስራ ፈጠራ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ ሰልጣኞችን ወደስራ ለማስገባት የቢዝነስ ፕላን ውድድር በማካሄድ የተሸለ የቢዝነስ ፕላን ላዘጋጁት አስር ቡድኖች ሃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ የስራ እንቅስቃሴ እንዲቀይሩ የስራ ማስጀመሪያ ገንዘብ ድጋፍ በሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በሽልማቱ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው መድረኩን የከፈቱት አቶ ባህሩ ሻፊ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ምክትል ዲን እንደገለፁት ከተለያዩ የጎረቤት ሃገራትና ከሀገር ዉስጥ የመጡ አስራ አራት ቡድን ሰልጣኞች ባቀረቡት ቢዝነስ ፕላን ተወዳድረው አስሩ አሸንፈው ወደራሳቸው ስራና ወደመረጡት የሙያ መስክ እንዲገቡ በዛሬው እለት የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል ፡፡

አክለውም በየጊዜው ራሳችሁን በስልጠና በማብቃትና በማሻሻል በሚሰጣችሁ ገንዘብ የራሳችሁን ስራ ሰርታችሁ በርትታችሁ ነገ ወደ ኢንተርፕራይዝነት በመለወጥ ለሌሎችም የስራ እድል እንድትከፍቱ ይሁን ብለዋል፡፡

ሽልማቱን የሰጡት የኮሌጁ ዲን የሆኑት አቶ ሸለማ ንጉሱም የእንኳን ደስ አላችሁ ምኞታቸውን በመግለፅ የዛሬ አሸናፊዎች የቴክኒክና ሙያ ውጤቶች ናችሁ የተሰጠው ድጋፍም ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ ሀሳባቸውን በተግባር እንዲያውሉ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩና ለሌሎች የስራ እድል እንዲከፍቱ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል፡

በመጨረሻም ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሙያ ስልጠና ባሻገር የስራ ፈጠራ አቅምን በማሳደግ ሰልጣኞችና ሌሎች ተጠቃሚዎችን የራሳቸውን የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ የሚያስችሉ የስራ ፈጠራ ስልጠናዎችንና ድጋፎችን መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጠል ተናግረዋ::

   

      

.

Copyright © All rights reserved.

Created with