Announcement የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችና አመራሮች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችና አመራሮች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

05th August, 2025

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችና አመራሮች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች እና አመራሮች "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 700ሚልዮን ችግኝ ተከላ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት በተካሄደው መርሀ ግብር ዐሻራቸውን አኑረዋል።
የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ: አረንጓዴ አሻራችን ሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን እንቅስቃሴ የሚደግፍ ነው ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የማህበረሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ነድፎ ከሚያከናውናቸው ቁልፍ የልማት ዘርፎች መካከል አንዱ አረንጓዴ ዐሻራ መሆኑን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ኮሌጁ ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የምታደርገውን ግስጋሴ በዘላቂነት ለመደገፍ የሚያስችሉ ቀጣይነት ያላቸው መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡
ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ



May be an image of 11 people, grass and tree
May be an image of 12 people and treeMay be an image of 1 person and grass
.

Copyright © All rights reserved.

Created with