የካቲት 11/2018
አዲስ አበባ — የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች ከጃይካ (JICA) ኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በኮሌጁ እየተተገበረ የሚገኘውን የካይዘን (Kaizen) ፍልስፍና አፈጻጸም ገመገሙ።
በውይይቱም ኮሌጁ የካይዘን ፍልስፍናን ከስርዓተ ስልጠናው ጋር በማያያዝ እየተሰጠ መሆኑን እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የካይዘን ድጋፍ በፕሮግራም እየተመራና ለውጥ እያመጣ መሆኑን ታይቷል።
በምክክር መድረኩ ላይ በኮሌጁ ውስጥ የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዘዴዎችን (ካይዘን) ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የታዩ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የጃይካ ተወካዮች የኮሌጁን የካይዘን ትግበራ ሂደት በአካል ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን፣ በቀጣይም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናውን ጥራት ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።




.