Announcement የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የGrand Africa Reward ተሻለሚ ሆነ ።

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የGrand Africa Reward ተሻለሚ ሆነ ።

28th July, 2025

እንኳን ደስ አላችሁ
በ2022 ዓ.ም በሙያዊ ክህሎቱ የበቃ ባለሙያ እና በስራ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ኢንተርፕራይዝ የሚያፈራ ተቋም ሆኖ ማየት የሚል ራዕይን የሰነቀ ንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኪሌጅ በ2017 ዓ/ም የግራንድ አፍሪካን የተቋማትና አመራር ሽልማት ተሸላሚ በመሆኑ መላው የኮሌጃችን ማህበረስብ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ግራንድ አፍሪካን የተቋማትና አመራር ሽልማት አዳዲስና ዘመናዊ አሰራር የዘረጉ ፣የላቀና ተጨባጭ እድገት ላስመዘገቡ፣ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ጠንካራ ጅምር ላላቸው፣መልካም ስማቸውን ጠብቀው ለአመታት ለዘለቁ ፣የአመራር ልህቀት ላስመዘገቡ፣ማህበራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ እና በትጋት ለሰሩ ተቋማት የሚሰጥ ሽልማት ነው፡፡
ተቋማችን ይህንን ውጤት ያገኘው የአይሶ 21001፡2018 የሰርተፊኬት ባለቤት በሆንበት ዓመት በመሆኑ ድርብ ደስታ እየተሰማን አሁንም ከምንግዜም በላይ ጠንክረን በመስራት ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ በማፍራት በሀገራችን እድገት የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንደምናደርግ እናበስራለን፡፡
ተልእኮአችን
በአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰቡንና ኢንዱስትሪውን በማሳተፍ ውጤት ተኮር ስልጠና በመዘርጋት ብቁ፣ ተወዳዳሪና የፈጠራ ክህሎት ያለዉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍና የቴክኖሎጂ ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር አገልግሎቶችን በመስጠት የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፣ የኢንዱስትሪውንና የከተማዋን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡
ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልህቀት ኮሌጅ


May be an image of map and text

.

Copyright © All rights reserved.

Created with