Announcement በኤል ሶሌእ ና ኢፍሶ በትብብር ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስልጠና ተሰጠ

በኤል ሶሌእ ና ኢፍሶ በትብብር ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስልጠና ተሰጠ

01st December, 2025

በኤል ሶሌእ ና ኢፍሶ በትብብር ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ከ17/03 /2018 እስከ 19/03/2018 ዓ/ም በኤል ሶሌ ና ኢፍሶ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በጎዳ ና ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ በስርዓተ-ፆታ ማካተት እና መገለልን እንዴት መቀነስ ይቻላል ( Workshop on Gender Inclusion and Reducing Stigma towards Youth in Street Situations) የሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለ120 በኮሌጁ ውስጥ ከሚገኙ ሁሉም የሰራ ክፍሎች ለተወጣጡ አሰልጣኞችና ዳይሬክቶሬት ስልጠና ተሰጥተዋል፡ ፡
የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ሸለመ ንጉሱ በስልጠና ቦታው በመገኝት የስልጠና አሰጣጡን የተመለከቱና በቀጣይ የኮሌጁ ማህበረሰብ ሁሉንም አገልግሎቶችን በሚንስጥበት ጊዜ ስርዓተ-ፆታ ባማከለ መልክ ስልጣኞችን እና ሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎችን ያለ አድሎ ማገልገል የእለት እለት ተግባራች መሆን እንደላበት እና ከኤል ሶሌና ኢፍሶ በጎ አድራጎት ድርጅት በጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶችን ከጎዳና ህይዎት እንዲላቀቁና የሙያ ባለቤትና ስራ ፈጣሪ ትውልድ እንዲሆኑ ከኮሌጃችን ጋር በተከታታይ እየሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታና በቀጣይም ከድርጅቱ ጋር አብረን በርካታ ስራዎችን ለመስራት ፍላጎት አለን በማለት ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ስልጣኞችም እንዴት ሰርዓተ- ፆታን በእቅዶቻችን እና በእለት እለት ተግባሮቻች ላይ ማካተት እንዳለብ፤ የጎዳና ተዳዳሪ ወጣቶች እንዴት መርዳት እንችላለን ፤ በማስልጠኝ ክፍሎች አካታች ትምህርት እንዴት መስጠት እንዳለበትእና በስልጣና ወቅት የክፍል ልምምዶች መከናወኑ ተጨማሪ እውቀት እንደጨመረላቸው እና በስልጠና አሰጣጥ ዘዴው ላይ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን አስረድተዋል ፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with