Announcement የ2017 ዓ.ም በጀት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

የ2017 ዓ.ም በጀት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

23rd July, 2025

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም በጀት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አከሄደ።
==============
ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
በ2017 በጀት ዓመት በቁልፍ ና አበይት ተግባራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ከኮሌጁ ማህበረሳብ ና ባለድርሻ አከላት እንዲሁም የሰራ ና ክህሎት ፅ/ቤት የዘርፉ ኃላፊዎች ና አስተባባሪዎች በተገኙበት የቴክኖሎጂ ልማት ና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አግልግሎት ም/ዲን በአቶ ባህሩ ሻፊ ሪፖርቱ ቀርቦ ውይይት ተድርጓል ።
በውይይቱ የአካዳሚክ ጉደዮች ም/ዲን ወ/ሮ መስከረም አስፈው የስልጠና ጥራት ለማስጠበቅ በጋራ ና በቅንጅት ስራዎች ማስረት የስፈልጋል ብሎዋል ።
ውይይቱን የመሩት የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የስልጠና ጥራት በማሳደግ ና የኢንተርኘራይዞችን ምርት ና ምርታማነት በማሳደግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ በመሰራቱ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች
- በ4ኛ ሀገር አቀፍ ክህሎት ውድድር በቴክኖሎጂ 1ኛ ደረጀ ተሻለሚ መሆን መቻሉ።
- በጥናት ና ምርምር በ2ኛ ደረጀ ተሻለሚ
-የISO ሰርትፊኬሽን ማግኘቱ።
-የአፈሪካ ሊደርሺኘ ግራንድ ሪወርድ ተሻለሚ መሆን መቻሉ
-የሌማት ትሩፈት ስራዎች ማስረቱ ና ሌሎች ስራዎች ተጨበጭ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል ።
በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት በጀት ዓመት ሲሆን ይህም ለቅንጅታዊ ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ ያስገኘው ውጤት ብሎዋል።
ቀጣይ በትኩረት የሚሰሩት ስራዎች
-የርፎርም ስራዎችን መጠናከር ።
-የቴክኖሎጂ፣ጥናት ና ምርምር ስራ መጠናከር
-የስልጠና ጥራትን መረጋገጥ።
-የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ።
-ካይዘን ቀጣይነቱ መረጋገጥ።
-ISO ተግበራዊ መድረግ
-የተቋም ልማት ስራዎች።
- ወርክሾፕ የማዘመን ስራ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱንና በቀጣዩ በጀት ዓመት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
May be an image of 3 people and dais
May be an image of one or more people

May be an image of 2 people, people studying, dais and text that says 'Source: Source:HDMI HDMI2 No NoSignal signal De'
May be an image of 3 people and dais
.

Copyright © All rights reserved.

Created with